Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት 9 ወራት ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ አከናወነ


ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት 9 ወራት ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ።

በስድስት ዘርፎች የተዋቀረው እና በሥሩ 44 ድርጅቶችን የያዘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የበጀት ዓመቱን የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

በተለያዩ የድርጅቶቹ አካባቢዎች በርካታ ተጽዕኖዎች ቢኖሩም ይህን ተቋቁሞ የሚሰራ አመራርና ሰራተኛ በመፈጠሩ ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ አመርቂ ውጤት እያመጣ መሆኑን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ገልጸዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽንና ማህበራዊ ኃላፊነት ዳይሬክተር አምባሳደር አሊ ሱለይማን በበኩላቸው፣ ተቋሙ ከሚሰራው የኢንቨስትመንት ሥራ በተጓዳኝ በሀገሪቱ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ አዎንታዊ ምላሾችን በሚገባ የተወጣበት በጀት ዓመት እንደነበርም ተናግረዋል።

በተለይም የሚድሮክ ድርጅቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ሁሉ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መስራት የተቋሙ ዋነኛ መገለጫ መሆኑንም አምባሳደር አሊ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል፣ ድርጅቶቹ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችም በበጀት ዓመቱ እንደፈተኗቸው ዳይሬክተሩ መግለፃቸውን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ መረጃ ያመለክታል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት 9 ወራት ከአጠቃላይ የምርት ሽያጭ ከ26 ቢሊየን ብር በላይ ማግኘቱም በውይይቱ ላይ ተጠቁሟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *