Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ሚኒስቴሩ በሥርዓተ ፆታ ጥቃት ተጎጂ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በግጭት የተጎዱ የሥርዓተ ፆታ ጥቃት ተጎጂ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል የስራ ውል ስምምነት ከዩኒሴፍ እና ከጄፓይጎ ጋር ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶችን ችግር በሚቀርፍ ጉዳይ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በተለይም ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እና ህፃናትን በተመለከተ ሲሰጣቸው የነበረውን ሁሉን አቀፍ አገልግሎት ለማሻሻል አሁን የተደረገው የውል ስምምነት ላይ ትኩረት ይደረግበታልም ነው ያሉት፡፡

ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን ለማገዝ ማገገሚያ ማዕከላት እንደገቡ እና በዘላቂነት እንዲያገግሙ ለማድረግ ስምምነት ከገባናቸው ተቋማት ጋር በጋራ እንስራለን ብለዋል፡፡

የዩኒሴፍ ተወካይ ዳውዳ ጉዊንዶ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችን በዘላቂነት እንዲያገግሙ ለማድረግ ዮኒሴፍ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል::

ዩኒሴፍ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ቤኒሻንጉል እና በሌሎችም ክልሎች ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች እያገዝ እንደሚገኝ ገልጸው አሁን የተደረገው ስምምነትም ይበልጥ ለመስራት ያግዘናል ብለዋል፡፡

ጄፓይጎ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ሸዋ ግርማ በበኩላቸው ጄፓይጎ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ዩኒሴፍ ጋር በጋራ በመሆን ፆታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ህጻናት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *