መቐለ ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት በ2013 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ የመጀመርያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችና የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አሰታወቀ።
ዩኒቨርስቲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ተመራቂ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለ2 ዓመታት ሲካሄድ የቆየውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አገልግሎት መስጠት ማቋረጣቸው አይዘነጋም።
ዩኒቨርሲቲው ከፌዴራል መንግሥት በተለቀቀለት በጀት ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችለውን ዕድሳት እና ተያያዥ ሥራዎችን አጠናቋል፡፡ በዚህ መነሻነት ከመጪው መስከረም አራት ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የመማር ማስተማር ሥራውን እንደሚጀምር መዘገባችን ይታወሳል።
