Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 ባለሃብቶች ውል ተቋረጠ


የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 90 ሄክታር መሬት በሊዝ ወስደው ያላለሙ 68 አልሚዎችን ውል ማቋረጡን እና 1 ሺ 283 አልሚዎች ግንባታ እንዲጀምሩ መወሰኑን አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም አስመልክቶ በተካሄደው ግምገማ ላይ እንደተናገሩት፤ አንዳንድ አልሚዎች መሬት ከተቀበሉ በኋለ በወቅቱ ግንባታ ሳይጀምሩ ለረጅም ዓመታት አጥረው ያስቀምጣሉ።

ነገር ግን የሊዝ ሕጉ አንድ መሬት ለልማት ከተወሰደ በኋላ መቼ እንደሚጀመር፤ መቼ ሀምሳ በመቶ መድረስና መቼ መጠናቀቅ እንደሚኖርበትም በግልጽ ያስቃምጣል ያሉት ዶክተር ቀነዓ፣ በዚህ መሠረት ግንባታው ካልተከናወነ ሕጉ መተግበር ስለሚኖርበት ቦታው መወሰዱ የማይቀር ነው ብለዋል።

እንደ ዶክተር ቀነዓ ገለጻ፤ አንዳንድ አልሚዎች ወደ ግንባታ ላለመግባታቸው እንደምክንያት የዋጋ ንረት፤ የግንባታ እቃዎችን ከውጪ ለማስገባት የውጪ ምንዛሪ እጥረት እንደሚገጥማቸው ያነሳሉ።

ኢፕድ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *