Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

ሕ.ወ.ሓ.ት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የቀረበውን የዕውቅና ጥያቄ ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በእነገ/ሚካኤል ተስፋዬ መካከል ሐምሌ 28 ቀን2015 ዓ.ም. በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ክርክር ችሎት የተደረገው ክርክር ውሣኔ ማግኘቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ፍርድ ቤቱ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቅድመ ዕውቅና ፍቃድ መጠየቃቸውን መጥቀሱ ተገልጿል፡፡

በተጠቀሰው ስያሜ የሚጠራ ለረጅም ዓመታት የሚታወቅ ፓርቲ የነበረ በመሆኑ፤ በዚሁ ስም አዲስ ፓርቲ ማቋቋም መራጩን የሚያደናግር መሆም ነው የተገለጸው፡፡

ቦርዱ ሰኔ 05 ቀን 2015 ዓ.ም. ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ተብሎ የሚጠራ ክልላዊ ፓርቲ ለመመሥረት የቀረበውን የቅድመ ዕውቅና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ስሕተት አይደለም በሚል የቦርዱን ውሣኔ እናዳፀና በማበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መረጃ አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *