ሃንጋሪ ከአውሮፓ ኅብረት ለዩክሬን መድረስ የነበረባቸው 544 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሣሪያዎችን ማገዷ ተሰማ።
መሳሪያው ከአውሮፓ ህብረት በአውሮፓ የሠላም ተቋም በኩል ለኪየቭ የሚላክ እንደነበር አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
ሃንጋሪ መሳሪያው “ዩክሬን ለማስታጠቅ ብቻ የሚውል ከሆነ” በእኔ በኩል አያልፍም ለዚህም ዋስትና ይሰጠኝ ስትል ጠይቃለች።
የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን አሜሪካ መራሹ የምዕራባውያን ጎራ ለዩክሬን በቡዳፔስት በኩል ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ማሳለፍ እንደማይችል ገልጸዋል።
ዋልታ
