Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ሀገራት በማዕድኑ ዘርፍ በኢትዮጵያ እንዲሠማሩ ጥሪ ቀረበላቸው

በኢትዮጵያ በማዕድኑ ዘርፍ በትብብር መሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

የኢፌዴሪ ማዕድን ሚኒስትር ሐብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፥ በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት እና ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሲ አነጋግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገራት የማዕድን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዘርፉ እንዲሰማሩ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ለአምባሳደሮቹ አብራርተዋል፡፡

አምባሳደሮቹም በሀገራቸው የሚገኙ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ በጋራ ለመሥራት ፈቃደኞች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ፋና


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *